Van Persie አሰልጣኝ ሆኖ ተመልሷል

ያጋሩት

የቀድሞ የአርሰናል እና የማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ ሮቢን ቫን ፔርሲ ከቀያይ ሰይጣኖቹ ጋር በቅርቡ ልምምድ እየሰራ የቆየ ሲሆን በአሰልጣኝነት ህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ትልቅ ክለብ ጋር ለመስራት የተዘጋጀ ይመስላል።

የ40 አመቱ ቫን ፔርሲ ወደ አሰልጣኝነት ጉዞው የጀመረው በአንጻራዊ በቅርብ ጊዜ በ2020 ሲሆን በመጀመሪያ የፌይኖርድ ክለብ ዋና የአጥቂዎች አሰልጣኝ በመሆን ሰርቷል። ቀጥሎም የክለቡን ታዳጊ ቡድን ይዞ እያሰለጠነ ነበር።

የኤሬዲቪዚው ክለብ ሄረንቪን በዚህ የውድድር ዘመን ችግር እየገጠመው ነው። እና እንደ ሆላንዳዊው ሚድያ AD ዘገባ ከሆነ ችግሩን የሚፈታው የቫን ፔርሲ ሊሆን ይችላል ብሏል። ቫን ፔርሲ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙም ገልጿል። ሄረንቪን በኔዘርላንድ ሊግ በ11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ፣ በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ለመሳተፍ ከጥሎ ማለፍ ደረጃ በ9 ነጥብ ዝቅ ብሎ ተቀምጧል።


ያጋሩት