ማንቸስተር ዩናይትድ ለሪያል ማድሪድ አጥቂን ሆሴሉን ለማስፈረምይፈልጋሉ። የ34 አመቱ ሆሴሉ በአሁኑ ሰአት ከኤስፓኞል በውሰት ወደ ሪያል ማድረድ ሄዷል። ሪያል ማድሪድ ለውሰቱ 500,000 ዩሮ የከፈለ ሲሆን በ1.5 ሚሊዮን ዩሮ የመግዛት አማራጭ አለው።
ሆሴሉ በዚው የውድድር ዘመን ጥሩ አቋም ላይ የሚገኝ ሲሆን በ38 ጨዋታዎች 13 ጎሎችን ሲያስቆጥር 3 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ሰጥቷል። ዩናይትዶች በክረምቱ የዝውውር መስኮት እሱን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተነግሯል። ሆሴሉ ከዚህ ቀደም እንደ ኒውካስል እና ስቶክ ሲቲ ባሉ ክለቦች ተጫውቷል።