Toni Kroos ኮንራቱን እስከ 2025 አራዘመ

ያጋሩት

ጀርመናዊው አማካኝ ቶኒ ክሮስ ኮንትራቱን እስከ 2025 በማራዘም ከሪያል ማድሪድ ጋር የሚያደርገውን ጉዞ ለመቀጠል ወስኗል። ይህ ዜና የወጣው ስለወደፊት ህይወቱ ለሳምንታት ግምቶች ሲወሩ ከቆየ በኋላ ነው። ከዚህ ቀደም የነበረው ኮንትራት በ2024 የሚያበቃ ነበር። ኮንትራቱ ሊጠናቀቅ ቢቃረብም ክሮስ በቅርብ ጊዜ ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር ባደረገው ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ብቃቱን ያሳየ ሲሆን በዚህም ምክያት ከማድሪድ ጋር ውሉን አራዝሟል።

በ2014 ሪያል ማድሪድን ከተቀላቀለ ወዲህ ከ450 በላይ ጨዋታዎችን በማድረግ እና በርካታ ዋንጫዎችን በማንሳት አራት የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን እና ሶስት የላሊጋ ሻምፒዮናዎችን ጨምሮ ለማድሪድ ክሮስ ቁልፍ ተጫዋች ነው። እንደ ጁድ ቤሊንግሃም እና ኤድዋርዶ ካማቪንጋ ያሉ አዳዲስ ችሎታ ያላቸው በማድሪድ የአማካይ ክፍል በአሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ እየተዋሃዱ ቢሆንም ክሮስ በዚህ ሲዝን በ20 የላሊጋ ጨዋታዎች ጉልህ ሚና መጫወቱን ቀጥሏል።

ምንም እንኳን 34 አመቱ ቢሆንም ክሮስ በላሊጋ በተጫወተባቸው ደቂቃዎች የረዥም ጊዜ የመሀል ሜዳ አጋሩን ሉካ ሞድሪች እንኳን በልጦ በሜዳው ላይ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ከጡረታ በወጣበት የጀርመን ብሔራዊ ቡድን በቅርቡ ያሳየው ብቃት ለሪያል ማድሪድም ሆነ ለብሔራዊ ቡድኑ ለዩሮ 2024 ሲዘጋጅ ያለውን ዘላቂ ጥራት እና አስፈላጊነት ይበልጥ አጉልቶ አሳይቷል።

ያጋሩት