ቶኒ ክሩስ ከጀርመኑ ዩሮ 2024 በኋላ ከእግር ኳስ አለም እንደሚሰናበት አሳወቀ። ኮከቡ የመሃል ሜዳ ተጫዋች ላለፉት 10 አመታት በሪያል ማድሪድ የቆየ ሲሆን ከዛ በፊት ደግሞ በ ባየርን ሙኒክ ነበር። ጫማ መስቀሉን በዚህ አመት ያደረገበት ምክያት የመጨረሻ ጨዋታው በሃገሩ ለማድረግ በማሰብ ነው።
ልብ በሚነካ ሁኔታ መልቀቁን በኢንስታግራም ያሳወቀው ክሩስ ከሪያል ማድሪድ ጋር የነበረውን ቆይታ እና ከደጋፊዎቹ ያገኘውን ድጋፍ አጸናኦት ሰጥቆበታል። ወደ ሪያል ማድሪድ የገባበትን ቀን ጁላይ 17 2004 ህይወት ቀያሪ ሲል ያስታውሰዋል። ክሩስ በክለቡ ወስጥ የሚገኙትን ሰዎች አሰመስኖ ሪያል ማድሪድ የመጨረሻው ክለብ እንደሚሆንም ተናግሯል።
ክሩስ በሪያል ማድሪድ ቆይታው 463 ጨዋታዎችን ተጫውቶ ብዙ ዋንጫዎችንም አንስቷል፤ እና ከክለቡ ጋር የመጨረሻ ጨዋታውን በተጠዋቂ የቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ከቦሪሺያ ዶርቱመድ ጋር ጁን 1 ላይ ይጫወታል። ከዛም በኋላ ለዩሮ 2024 ጀርመንን ወደመምራት ይሄዳል፤ እሱም ከ13 ቀን በኋላ ከ ስኮትላንድ ጋር ይጋጠማል። የክሩስ አስደናቂ የእግር ኳስ ህይወት ብዙ ዋንጫዎችን ያካተተ ነው ከእነሱም ውስጥ በ2014 ከጀርመን ጋር ያሸነፈው የአለም ዋንጫ፣ እና ለሎች የሊግ እና የ ኢንተርናሽናል ዋንጫዎች ያካትታል።