Ronaldo በቀይ ካርድ!

ያጋሩት

ሰኞ እለት አል ናስር በሳውዲ ሱፐር ካፕ የ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በአል-ሂላል 2-1 ሽንፈት ሲገጥመው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

የሮናልዶ ብስጭት የጀመረው በመጀመሪያው አጋማሽ መገባደጃ ላይ በፖርቹጋል ኮከብ ምክኒያት ቡድኑ ጎል ሲሻር ነበር። በኋላ ላይ የእጅ ኳስ ፈጥኖ ለማውጣት ሲል ከአልሂላል ተጫዋችጋ በተፈጠረው ንትርክ ቁጣው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ የአል-ሂላሉን ተጫዋች በክርን በመግጠም ሊማታ መሞከሩ ነበር ቀጥታ ቀይ ካርድ የተሰጠው – ይባስ ብሎም በዳኛው ላይ በቁጣ እጁን የምት ስንዝር አድርጎ ነበር።

የሳውዲ አረቢያ ሱፐር ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ውድድር አል ናስር 1ለ2 ተሸንፏል። ለሮናልዶ ቡድን ሳዲዮ ማኔ ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል። አል-ሂላል በአል ዳውሳሪ እና ማልኮም ግብ አስቆጥሯል።

በሳውዲ አረቢያ ሱፐር ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ አል ሂላል ከአል-ኢትሃድ ጋር ይጫወታል።

ያጋሩት