Olivier Giroud ወደ MLS አሜሪካ

ያጋሩት

ለሚላን እና ለፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድኑ የሚጫወተው አጥቂ ኦሊቪየር ጂሩድ ወደ አሜሪካ ለመዘዋወር እያሰበ ነው። ጂሩድ ወደፊት ለሚሆነው በማሰብ ለሚላን ወጣት አጥቂ እንዲያመጡ ሃሳቡን ገለጸ። ጂሩድ በማንኛዉም እንቅስቃሴ ውስጥ በጣም አስፈላጊው ነገር ልጆቹን የሚጠቅም ነገር ማድረግ መሆኑን ገልጿል፣ ማንኛውንም ውሳኔ ለማድረግ የቤተሰብ ጉዳዮች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ አጽንኦት ሰጥቷል።

“ወደፊት ምን እንደሚሆን አሁንም አላውቅም። በሚላን ደስተኛ እንደሆንኩ እና ትልቅ ስኬት እንዳስመዘገብን አውቃለሁ። በጣም ጥሩ የፍቅር ግዜ ነበር። እስካሁን ከክለቡ ጋር ስለ ማራዘሚያ አልተወያየንም፤ ወደ በኋላ ተወያይተን ውሳኔ እንወስናለን። በአሁን ሰአት አስገላጊው ነገር የክለቡ ጎሎች ነው።

ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ሊሄድ ስለሚችለው ነገር ሲጠየቅ መለሰ፡-

“ኤምኤልኤስ? ሌሎች አገሮችም አሉ። በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ላይ ብዙ እድሎች ይነሳሉ፣ እና ያኔ ውሳኔ እወስናለው። እንደ አባት እና እንደ እግር ኳስ ተጫዋች።”


ያጋሩት