Olivier Giroud ወደ MLS ሊሄድ ነው

ያጋሩት

ኤሲ ሚላን ታዋቂው ፈረንሳዊ አጥቂ ኦሊቪየር ጂሩድ በውድድር አመቱ መጨረሻ ቡድኑን እንደሚለቅ አሳወቁ። የጂሩድ ኮንትራት አይታደስም እና ከቀጣይ ክለቡ ጋር ሚያደርገው ዝውወር ነጻ ይሆናል።

ይፋዊው ማስታወቂያ ጂሩድ ኤላኤፍቺን ሊቀላቀል መሆኑን ገልጿል። ለአንድ አመት ተኩል ኮንትራት መፈራረሙ ተነግሯል እና ኮንትራቱ ካለቀ በኋል ኮንትራቱን የማራዘምም ምርጫ የፈረመው ኮንትራቱ ላይ ተካቷል።

ጂሩድ በ2021 ከቼልሲ ወደ ሚላን የተቀላቀለ ሲሆን በዚህ ሲዝን 16 ጎሎችን በማስቆጠር 9 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ቁልፍ ተጫዋች ሆኗል። በተለያዩ ክለቦች አስደናቂ ታሪክ ያለው እና የፈረንሳይ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የጂሩድ መሰናበት የሚላንን ዘመን ማብቃቱን ያሳያል።

ያጋሩት