ናይጄሪያ በ2024 የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ማለፏ ያረጋገጠችው ከደቡብ አፍሪካ ጋር ባደረገችው ውጥረት የተሞላ ግጥሚያ ነበር። የመጀመርያው አጋማሽ ጥንቃቄ የተሞላበት ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች ተመጣጥነው ነበር ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤትም ወደ እረፍት ገቡ። ስታንሊ ንዋቢሊ ከማክጎፓ በአደገኛው የተመታው ኳስ በጥሩ ሁኔታ ያዳነበት አስደናቂ ትእይንት ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ ናይጄሪያ የፍፁም ቅጣት ምት አግኝታለች ዊልያም ትሮስት-ኤኮንግ ምንም ሳይቸገር በልበ ሙሉነት ወደ ጎል ቀይሮታል። ናይጄርያም አንድ ለባዶ መምራት ቻለች።
ናይጄሪያ ሁለታኛ ጎል ባስቆጠረችበት ወቅት ያልተጠበቀ ለውጥ ተፈጠረ ግቡ ተከልክላ በምትኩ ደቡብ አፍሪካ ፍፁም ቅጣት ምት ተሰጠች። ይህ ውሳኔ በ VAR ታይቶ የተደረገ ነበር። ከጎሉ በኋላ ናይጄሪያ ውጥረት ውስጥ ነበረች ደቡብ አፍሪካ በመደበኛው ሰአት ልታሸንፍ ትንሽ ተቃርባም ነበር። ነገር ግን መደበኛ ሰአት አለቆ ጨዋታውን ወደ ትርፍ ሰአት ቀጠለ በ115ኛው ደቂቃ ግራንት ኬካና በቀይ ካርድ በመውጣቱ ደቡብ አፍሪካ በአስር ተጨዋቾች ለመጫዎት ተገደደች። ናይጄሪያ ይህን ብልጫ ብታገኝም ሳታሸንፍ ጨዋታው ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ተሻገረ። ፍፁም ቅጣት ምቱ አራት በሁለት የሆነት ውጤት ናይጄርያ አሸነፈች። የናይጄሪያው ግብ ጠባቂው ዋቢሊ ሁለት ምቶችን በማዳን ናይጄርያ ወደ AFCON ፍፃሜ እንድታልፍ አድርጓል።
ናይጄሪያ ለፍፃሜ አይቮሪ ኮስትን እሁድ የካቲት 11 2024 ትገጥማለች።
AFCON, ግማሽ ፍፃሜ
Nigeria – South Africa 1:1 4:2 penalties
Goals: Troost-Ekong, 67 (penalty) – Mokoena, 90 (penalty)
Red card: Kekana, 115