ሪያል ማድሪድ ለቡድኑ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ትሬንት አሌክሳንደር-አርኖልድን ከሊቨርፑል ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ለረጅም ጊዜ ሲጫወትላቸው ለቆየው ለዳኒ ካርቫጃል ጥሩ ምትክ አድርገው ይመለከቱታል። ሌላኛውን ተጫዋች ሪስ ጀምስን ለማስፈረም ፈልገው ነበር ነገር ግን በጉዳት ብዛት ምክያት ሃሳባቸውን ቀይረዋል።
ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑልን አሌክሳንደር አርኖልድን መግዛት ይችሉ እንደሆነ አልጠየቁም። የእሱ ውል ምን እንደሚሆን ለማየት ረያል ማድሪድ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። አሁን ከሊቨርፑል ጋር ያለው ውል በ2025 የሚያልቅ ቢሆንም በአዲስ ስምምነት ላይ ግን አልተስማሙም።
አሌክሳንደር-አርኖልድ ከ2016 ጀምሮ ለሊቨርፑል እየተጫወተ ይገኛል። በዚህ የውድድር ዘመን 2 ጎሎችን አስቆጥሮ የቡድን አጋሮቹን በ29 ግጥሚያዎች 10 ጊዜ ግብ እንዲያስቆጥሩ ረድቷል። ግን ከፌብሩዋሪ 13 ጀምሮ በጉልበት ጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ውጪ ሆኗል።