መሪነቱን ያሳጣው የ Liverpool ሽንፈት

ያጋሩት

ሚያዝያ 14 2024 ሊቨርፑል ክሪስታል ፓላስን በአንፊልድ አስተናግዷል። ይህ ግጥሚያ ለመርሲሳይዱ ክለብ በዋንጫ ውድድር ላይ ትልቅ ትርጉም ነበረው ቢሆእም ነገርግን የጨዋታው ውጤት ያልተጠበቀ ሆኖ ተገኝቷል።

በ14ኛው ደቂቃ ላይ እንግዳዎቹ ክሪስታል ፓላስ ጎል ማስቆጠር የቻሉ ሲሆን በጨዋታውም ላይ የታየው ብቸኛዋ ጎል ነበረች። ቀያዮቹ ብዙ አይነት የማጥቃት ሙከራ ቢያደርጉም በክሪስታል ፓላሱ ዲን ሄንደርሰን የተከለለውን ጎል ማስገባት አልቻሉም። የ ክሪስታል ፓላሱ ኪፐር 6 የጎል ሙከራዎችን አድኗል። ሊቨርፑል በእርግጠኝነት ብዙ ጎሎችን ለማስቆጠር በጥሩ ሁኔታ ተጫውቷል ፣ ለሊቨርፑል የተጠበቀውም የ ጎል ሬሾ (xG) 2.97 ነበር። ሆኖም ዕድሉ በዚያ ሜዳ ከየርገን ክሎፕ ሰዎች ጎን አልነበረም።

ከጨዋታው በኋላ ጀርመናዊው አሰልጣኝ ቡድናቸው በመጀመሪያው አጋማሽ ባሳየው ብቃት ማዘናቸውን ገልፀው ነገር ግን አሁንም 6 ጨዋታዎች እንደሚቀሩት እና ሊቨርፑል እስከመጨረሻው ትግሉን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። ሊቨርፑል በአሁኑ ሁኔታ 71 ነጥብ ይዞ በሶስተኛነት ማንሲትን እና አርሰናልን እየተከተለ ይገኛል።

33ኛው ዙር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ
Liverpool 0-1 Crystal Palace
Goal: Eze 14.


ያጋሩት