በ16ኛው ዙር የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) ጨዋታ ሴኔጋል ከአይቮሪኮስት ጋር ተገናኝታለች። ጨዋታው የተካሄደው ሰኞ ጥር 29 ቀን ነው። የሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን ፈጣን ጎል በማስቆጠር ቀዳሚ ተጽኖ አድርጓል። በጨዋታው አራተኛው ደቂቃ ላይ ሀቢብ ዲያሎ ብሄራዊ ቡድኑን ቀዳሚ አድርጓል። የመጀመርያው አጋማሽ አይቮሪ ኮስት የበለጠ የኳስ ቁጥጥር ቢያደርግም ሁለቱም ቡድኖች በድጋሚ ጎል ማስቆጠር አልቻሉም።
በሁለተኛው አጋማሽ አይቮሪኮስት የኳስ ሜዳውን መቆጣጠሯን ቀጥላ ቡድኑን አቻ ማድረግ የምትችልበት ዕድሎች ፈልጋለች። በ83ኛው ደቂቃ የሴኔጋሉ ግብ ጠባቂ ኤዶዋርድ ሜንዲ በሰራው ፋወል ለአይቮሪ ኮስት ፍፁም ቅጣት ምት አስገኝቷል። ፍራንክ ኬሲ በልበ ሙሉነት ወደ ግብነት ቀይሮ ጨዋታውን አቻ በማድረግ ወደ ተጨማሪ ሰአት ወሰደው።
የጭማሬ ሰአቱ ለደጋፊዎች ምንም ግብ አላመጣም። ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ተሸጋገሩ። በፍፁም ቅጣት ምት የአይቮሪ ኮስት ተጫዋቾች የበለጠ ብቃት አሳይተዋል አራት ለሰዎስት በሆነ ውጤትም አለቀ። “ዝሆኖቹ” ሴኔጋልን ፈታኝ በሆነ ጨዋታ አሸንፈው ወደ ሩብ ፍፃሜው አልፈዋል።
Senegal (ሴኔጋል) 1 – 2 Ivory Coast (አይቮሪ ኮስት)