Ivory Coast ጨዋታው ቀልብሳ ወድ ግማሽ ፍፃሜ አለፈች

ያጋሩት

በአስደናቂው የሩብ ፍፃሜ አፍሪካ ዋንጫ (AFCON) ጨዋታ አይቮሪ ኮስት ማሊን 2-1 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜው መቀላቀል ችላለች። ቀድሞ የተሻለ አቋም ያሳየችው ማሊ ያገኘችው ፍፁም ቅጣት ምት መጠቀም አልቻለችም። ከእረፍት መልስ ማሊ በተሻለ ተጫውታለች ጥሩ ዕድሎችንም አግኝታ ነበር። 

ማሊዎች ጥረታቸው ፍሬ ማፍራት የቻለው በ71ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው ኔኔ በርካታ ተጋጣሚዎችን አልፎ አይቮሪኮስት ላይ ጎል አስቆጥሯል። በስታዲየሙ ውስጥ የነበሩት የኮትዲቫር ደጋፊዎች ተስፋቸውን ጨርሰው ሊወጡ በሚሉበት ሰአት አይቮሪኮች የአቻ ግብ በማግባት ጨዋታውን ወደ ትርፍ ሰአት መውሰድ ችለዋል። በጭማሬው ሰአት የመጨረሻዎቹ ሰኮንዶች ውስጥ ባለሜዳዎቹ ኮኦትዲቫሮች ግብ አግብተው ድሉን በመንጠቅ ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፈዋል።

Mali – Ivory Coast — 1:2

Goal: Nene 71 — Adingra 90, Diakite 120+2.


ያጋሩት