ማንቸስተር ሲቲ ከኤቨርተን ትላንትና ጨዋታ ነበራቸው። ሲቲ ያለፉትን 9 ጨዋታዎችን በማሸነፍ ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ነበር ነገርግን ኤቨርተን በስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም ጥሩ እንቅስቃሴ አልነበራቸውም። ጨዋታው ኤቨርተን አቻ ለመወጣት የተለየ ነገር እንደሚያስፈልገው አሳይተው ነበር።
በጨዋታው ሁሉ ማንቸስተር ሲቲ የበለጠ እያጠቁ ነበር። ብዙ የጎል እድሎችን መፍጠር ባይችሉም ከኤቨርተን የበለጠ በማጥቃት ላይ ነበሩ።
የጨዋታው ኮከብ ከማንቸስተር ሲቲው ኤርሊንግ ሃላንድ ነበር። ለተወሰነ ጊዜ ጎል አላስቆጠረም ነገርግን በዚህ ጨዋታ ወደመጨራሻዎቹ ሰአታት ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል። ያስቆጠራቸው ግቦች ማንቸስተር ሲቲ ጨዋታውን 2-0 እንዲያሸንፉ ረድቷቸዋል።