በ16ኛው የአፍሪካ (AFCON) ዋንጫ ግብፅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ነበር የገጠመችው። ሁለቱም ቡድኖች ከምድባቸው በሶስት የአቻ ጨዋታዎች በአንድ ነጥብ ካለፉ በኋላ ነው የገጠሙት። ግብፅ እና ኮንጎ በመጀመርያው አጋማሽ አንድ አንድ ጎሎች ተለዋውጠው የአቻ ውጤት በመያዝ ወደ እረፍት ገቡ። ግብፅ በጭማሪ ሰአት ወደ አስር ተጫዋቾች ብትቀነስም ኮንጎ መጠቀም ተስኗት ጨዋታው ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ቀጠለ።
በፍፁም ቅጣት ምቱ ሁለት ተጨዋቾች ብቻ ኳሶችን አምክነዋል፡ ሙስጣፋ እና ማሱኩ መረብን ማግኘት አልቻሉም። ግብ ጠባቂዎቹ ወሳኝ ሚና የተጫወቱ ቢሆኑም የግብፁ ግብ ጠባቂ ጋባስኪ የመታው ኳስ የጎል ብረቱ መትቶ በመውጣቱ ግብፅ ልትሸነፍ ግድ ሆነ። ኮንጎው ወደ ሩብ ፍፃሜው በማለፏ የካቲት 2 2024 ላይ ከጊኒ ጋር ለግማሽ ፍፃሜው ቦታ ትገጥማለች።