ቼልሲ አስቶንቪላን አሸንፈው ወደ አምስተኛው ዙር ኤፍኤ ዋንጫ በቀላሉ ማለፍ ችለዋል። የኮኖር ጋላገር ቀድሞ ያስቆጠራት ጎል ጨዋታው ለቼልሲ ጥሩ መስመር ሲያሲዝ ኒኮላስ ጃክሰን እና ኤንዞ ፈርናንዴዝ ጎሎችን ጨምረው የቼልሲን መሪነት አስጠበቁ። ቪላ የጎል እድሎችን ቢያገኝም አልተጠቀመበትም መከላከል ላይም ተቸግሮ ነበር ይህም ጃክሰን በቀላሉ ጎል እንዲያገባ አስችሎታል። ቪላ ዘግይቶ የማበረታቻ ጎል ቢያስቆጥርም የቼልሲን አሸናፊነት ለመቀልበስ በቂ አልነበረም።
በቅርብ ጊዜ በፕሪሚየር ሊግ ሽንፈት ቢገጥመውም፣ ቸልሲ ቀርፋፋ ብሎ ከተጫወትው ቪላ የታሻለ ንቃት እና ቁጥጥር አሳይቷል። ቼልሲን ይለቃል ተብሎ ሲነገር የነበረው ፈርናንዴዝ አስደናቂ ጨዋታ ያሳየ ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ ፈርናንዴዝ ድንቅ ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሏል። ቼልሲ በዚህ ወር መጨረሻ በ FA CUP ሩብ ፍፃሜው ሊድስ ዩናይትድን ይገጥማሉ።
Aston Villa vs Chelsea: 1 – 3