Arsenal የ Gabriel Jesus ን ዝውውር እይሰቡበት ነው

ያጋሩት

አርሰናል ጋብሪኤል ጄሱስን በዚህ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሊሸጡት ፍቃደኛ ናቸው ሲል ዘገባዎች ይናገራሉ። ብራዚላዊው አጢቂ በ2022 ከማንቸስተር ሲቲ የተቀላቀለ ሲሆን በጉልበቱ ላይ ባጋጠመው ጉዳት አብዛኛውን የውድድር ዘመን ከሜዳ እንዲርቅ አድርጎታል። በዚህ የውድድር ዘመን እንደባለፈው የውድድር ዘመን ጎል ለማግባት ተቸግሯል ፤ እናም ለግዜው አሰልጣኙ ሚኬል አርቴታ በአጥቂ ቦታ ካይ ሃቨርትዝን መርጧል።

ኮንትራቱ ሊጠናቀቅ ሶስት አመት ቢቀረውም አርሰናል ለጄሱስ የመጣለትን ጥያቄ ሊመለከቱ ይችላል። ጎል ማስቆጠር የሱ ጠንካራ ጎኑ እንዳልሆነ በማመኑ ትችት ገጥሞታል፣ እና ቀጣይነት ያለው የጉልበት ጉዳይ በአጨዋወቱ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል። በሃቨርትዝ እምቅ ሃይል ፣ ጄሱስ በመጀመርያ አሰላለፍ ቦታውን ማስመለስ ከባድ ሆኖ አግኝቶታል በዚይም ምክያት ዝውውሩ ተስፋ ያለው ይመስላል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሃቨርትዝ አስደናቂ ብቃት አርሰናልን በፕሪሚየር ሊጉ አናት ላይ እንዲቆይ አድርጎታል ምንም እንኳን ማንቸስተር ሲቲ ቀሪ ጨዋታ ቢኖረውም። ጄሱስ ተጠባባቂ ወንበር ላይ እያለ አርሰናል በርንማውዝን ይገጥማል እና የክረምቱ የዝውውር መስኮት እየተቃረበ ሲመጣ ምናልባትም በቡድናቸው ስብስብ ላይ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።

ያጋሩት