Arsenal በፕሪምየር ሊግ የኖቲንግሃም ፎረስትን አሸንፏል

ያጋሩት

በ22ኛው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አርሰናል ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ተፋጧል። በመጀመርያው አጋማሽ የኳስ ቁጥጥር ቢያደርጉም አርሰናል በቀድሞው ግብ ጠባቂያቸው የነበረው ማት ተርነር ላይ ያገኙት የጎል እድሎች ወደ ግብነት መቀየር ተስንዋቸው ሲቸገሩ ተስተውሏል። 

ነገርግን በሁለተኛው አጋማሽ የአርሰናል የማጥቃት ጫና እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ጋብሬል ጂሰስ ጎል አስቆጥሯል። ቡካዮ ሳካ ብዙም ሳይቆይ መሪነቱን በማስፋት የአርሰናልን ብልጫ አስገኝቷል። ኖቲንግሃም ፎረስት በ ታይዎ አኒዪን ዘግይቶ አንድ ብያስቆጥሩም አርሰናል መሪነቱን አስጠብቆ ወሳኙን ድል አስመዝግቦ በ46 ነጥብ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የሚኬል አርቴታ ቡድን በየካቲት 4 2024 ከሊቨርፑል ጋር ትልቅ ፈተና ይገጥመዋል።

Premier League, 22nd Round Nottingham Forest – Arsenal – 1:2 Goals: Awoniyi, 89 – Jesus, 65, Saka, 72

ያጋሩት