አርሰናል በዚህ የክረምት የዝውውር መስኮት ጎበዝ አጥቂ ማስፈረም ይፈልጋሉ፤ የኒውካስሉ አሌክሳንደር ኢሳክ ትልቁን ኤላማ ቢስብም። ሆኖም፤ አርሰናል ኢሳን ማስፈረም ሊከብዳቸው ይችላል ምንያቱም ኒውካስል ኮከብ ተጫዋቻቸውን መሸጥ ስላማይፈልጉ። እንደ ሁለተኛ አማራጭ፣ አርሰናል 22 ግቦች እና 12 አሲስቶች ያለውን በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘውን የአያክሱን ብሬን ብሮቤይ እየተመለከቱ ይገኛሉ።
አርሰናል ሁለቱንም ኢሳክን እና ብሮቤይን ማስፈረም ካልቻለ ሶስተኛ አማራጫቸው የስፖርቲንግ ሲፒው ቪክቶር ግዮከርስ ነው። ግዮከርስ በዚህ የውድድር ዘመን አስደናቂ አቋም ቢኖረውም ከለቡ ስፖርቲንግ ሲፒ ጣራ የነካ የዝውውር ዋጋ ይጠይቃሉ እሱም €100m ነው። እና አርሰናል ከነዚህ አንዱን በማስፈረም ለቀጣዩ የውድድር ዘመን የአጥቂ ክፍላቸውን ያጠናክራሉ።