ማንቸስተር ዩናይትዶች ስለ አንቶኒ ማርሻል አለመገኘት ወቅታዊ መረጃ አቅርበዋል አጥቂው በብሽት (Groin) ጉዳት ቀዶ ጥገና ማድረጉን ገልጸዋል። በህመም ምክንያት ከዲሴምበር መጀመሪያ ጀምሮ መጫወት ያልቻለው ማርሻል አሁን ከሁለት ወር በላይ ከሜዳ እንደሚርቅ ታውቋል። ክለቡ በፍጥነት እንዲያገግም ቢመኝም በኤፕሪል አጋማሽ ብቻ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ሰባት ጨዋታዎች ያመለጡበት ማርሻል የፕሪሚየር ሊጉ የውድድር ዘመን ከመጠናቀቁ በፊት ተመልሶ የሚመጣበት እድል ጠባብ ነው። አሁን ያለው ኮንትራት በክረምቱ የሚጠናቀቅ ሲሆን ምንም እንኳን ለ12 ወራት ማራዘሚያ አማራጭ ቢኖርም ማንቸስተር ዩናይትድ ውሉን እንደሚያስነሳው እርግጠኛ አይደለም። የ28 አመቱ ተጫዋች በኦልትራፎርድ ከ9 አመታት በኋላ ክለቡን በነፃ ሊለቅ ይችላል።
ወደ ፊት ስንመለከት ማንቸስተር ዩናይትዶች በክረምቱ የዝውውር መስኮት አዲስ አጥቂ ለማግኘት እያሰቡ ነው። ትኩረቱ ራስሙስ ሆጅሉንድን የሚደግፍ ልምድ ያለው ተጫዋች ማፈላለግ ላይ ነው ነገርግን የ21 አመቱ የአያክስ አጥቂ ብሪያን ብሮቢ በአሁኑ ሰአት የክለቡ ኢላማ እንዳልሆነ ተነግሯል።