የ United ን አይን የሳበው Ivan Toney

ያጋሩት

ማንቸስተር ዩናይትዶች የአጥቂ አማራጮቻቸውን ለማሳደግ ከብሬንትፎርድ ኢቫን ቶኒ ማስፈረም ይፈልጋሉ። በዚህ ክረምት ወይም በ2025 ሊለቅ የሚችለው ቶኒ £50m አካባቢ ሊወጣበት ይችላል። ዩናይትድ እሱን መሪ እንደሚሆን በልበ ሙሉነት ያዩታል ነገርግን እንደ ቤንጃሚን ሴስኮ ከ አርቢ ላይፕዚግ ያሉ ሌሎች አማራጮችን ይመለከታሉ።

የቶኒ ዋጋ አነሰ ከተባለ እስከ £30m ወይም በዛ ከተባለ እስከ £100m ሊደርስ ይችላል። ከብሬንትፎርድ ጋር መደራደር ቀላል አይሆንም ነገርግን ዩናይትዶች በበጀታቸው ስምምነት ለማድረግ ተስፋ ያደርጋሉ። ቼልሲ እና አርሰናልም ቶኒን እየፈለጉ ይገኛሉ ነገርግን አርሰናል የሚመርጠው ወጣት አጥቂዎችን ነው። የቶኒ የደመወዝ ጥያቄ በሳምንት £250,000 ሊደርስ ይችላል።

ከእገዳው በኋላ ቶኒ በብሬንትፎርድ እና በእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ጎሎችን አስቆጥሮ ጠንክሮ ተመልሷል። ዩናይትዶች እሱን እንደ ቁልፍ ተጫዋች ይመለከቱታል ነገርግን ድርድሮች በመካሄድ ላይ ናቸው እና ሌሎች ክለቦችም ፍላጎት አሳድረውበታል።

ያጋሩት