ሰኞ የካቲት 5 2024 የ23ኛው ዙር አካል የሆነው ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ ብሬንትፎርድን ሊገጥም ተጉዞ ነበር። በመጀመርያው አጋማሽ ምንም እንኳን ሲቲ ብዙ የኳስ ቁጥጥር ቢያደርግም ብሬንትፎርድ ነበር መሪነቱን የወሰደው። በ21ኛው ደቂቃ የብሬንትፎርዱ ምቤውሞ(Mbeumo) ከግብ ጠባቂው የተላከውን ኳስ ጎል አስቆጠረ። ነገርግን ብሬንትፎርድ መሪነቱ እስከ እረፍት ማስጠበቅ አልቻለም። በጭማሬው ሰአት ሶስተኛው ደቂቃ ላይ ፊል ፎደን ጎል አስቆጥሮ ሲቲን አቻ አድርጓል።
ከእረፍት መልስ እንግሊዛዊው አማካኝ ፎደን ድንቅ እንቅስቃሴውን ቀጠለ። በ53ኛው ደቂቃ ፎደን ለሲቲ ሁለተኛው ጎል አስቆጠረ። ሲቲዎች የበላይነታቸውን የቀጥለው 70ኛው ደቂቃ ላይ በድጋሜ ፎደን ጎል አስቆጥሮ ሃትሪኩን ሰራ። ጭዋታው ብሬንትፎርድን አንድ ማንቸስተር ሲቲ ሶስት በሆነ ውጤት ተጠናቀቀ። ማንቸስተር ሲቲ ከ22 ጨዋታዎች በኋላ በ49 ነጥብ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።