ለአንድ አመት ከቼልሲ በውሰት ወደ ሮማ የመጣውን ሮሜሉ ሉካኩን ሮማ በቋሚነት በቡድናቸው ለማቆየት ወይም ለመልቀቅ መወሰን ነበረባቸው። በ41 ጨዋታዎች 18 ጎሎችን በማስቆጠር ጥሩ ግዜ እያሳለፈ ይገኛል ነገርግን ሮማዎች ቼልሲ ለሱ በሚፈልገው ከፍተኛ ዋጋ ምክንያት ላያስፈርሙት ይችላል።
ቼልሲዎች ሉካኩን በ37 ሚሊየን ፓውንድ እንደሚሸጡት ቢናገሩም ሮማ ግን በጣም ብዙ ነው ብለው ያስባሉ። ሉካኩ ለደሞዙም ብዙ ገንዘብ ጠይቋል፤ ይህም የበለጠ ውድ ያደርገዋል። ሉካኩ ከሮማ ጋር መቆየት ቢፈልግም ክለቡ ወደ ቼልሲ ሊመልሰው ይችላል።
ሮማ ሉካኩን ካላስፈረሙ ለቼልሲ አዲስ አጥቂ ለማግኘት ሊረዳቸው ይችላል። ቼልሲዎች እንደ ቪክቶር ኦሲምሄን ከናፖሊ ውድ የሆኑ ተጫዋቾችን እና ቤንጃሚን ሴስኮ ከ አርቢ ሌብዚግ በርካሽ አማራጭ ሊሆኑ ይችላሉ።