ባየር ሊቨርኩሰን እና አታላንታ በሜይ 22 / ግንቦት 14 በዱብሊን አቪቫ ስታዲየም በዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ይጫወታሉ። በዣቪ አሎንሶ የሚመራው ሊቨርኩሰን አስደናቂ የውድድር ዘመን ያሳለፈ ሲሆን የቡንደስሊጋውን ዋንጫ በማንሳት ቀጥሎ ደግሞ ትሬብል ለመብላት ጉዞ ላይ ናቸው። በግማሽ ፍፃሜው ሊቨርኩዘን ከሮማ ከባድ ፈተና ገጥሞት የነበረ ቢሆንም በጆሲፕ ስታኒሲች በመጨረሻ ሰአት ባስቆጠረው ጎል ለፍጻሜ መድረሱን ማረጋገጥ ችሏል።
በአንፃሩ አታላንታ ብዙ ጊዜ የመውረድ ታሪክ ቢኖረውም ለመጀመሪያ ግዜ የአውሮፓ የፍፃሜ ጨዋታ ደርሳለች። ማርሴይን በማሸነፍ በአሰልጣኝ ጂያን ፒዬሮ ጋስፔሪኒ ያገኙትን ስኬት አሳይተዋል። አትላንታ በአውሮፓ ውድድሮች የምታደርገው ጉዞ በ2020 የቻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ እና በ2022 የኢሮፓ ሊግ ሩብ ፍፃሜ መድረሱን ያጠቃልላል።
የፍጻሜው ተስፋዎች የተለያየ ታሪድ ያላቸው ነገር ግን ለአውሮፓ ክብር ተመሳሳይ ምኞት ባላቸው ሁለት ቡድኖች መካከል አስደሳች ፍልሚያ ይሆናል። ሌቨርኩሰን ልዩ የውድድር ዘመኑን በሶስት ዋንጫ ለመጨረስ ይፈልጋሉ፣ አትላንታ ግን የመጀመሪያውን የአውሮፓ ትልቅ ዋንጫ በማንሳት ታሪክ ለመስራት አስበዋል።