በአስደናቂው ጨዋታ ቼልሲዎች ማንቸስተር ዩናይትድን በአስተራሚ አጨዋወት ውጤቱን ቀልብሰውት 4-3 ማሸነፍ ችለዋል፤ ኮል ፓልመር በጨዋታው መገባደጃ ደቂቃዎች ላይ ሁለት ጎሎችንም አስቆጥሯል። ቼልሲዎች በመጀመሪያ 2-0 ቢመሩም ዩናይትዶች ነጥባቸውን 3-3 በሆነ ውጤት አቻ ማድረግ ችለው ነበር።
ጨዋታው ቼልሲዎች በኮኖር ጋላገር ቀድመው ሲመሩ ፓልመር ፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሮ መሪነቱን እንዲያሰፋ አድርጓል። ነገርግን ዩናይትድ ከእረፍት በፊት በአሌሃንድሮ ጋርናቾ እና በብሩኖ ፈርናንዴዝ ሁለት ጎሎች ጨዋታው አቻ እንዲሆን አድርገዋል።
በሁለተኛው አጋማሽ ዩናይትዶች በጋርናቆ ጎል መሪ ቢሆኑም ቼልሲዎች በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ፓልመር ባስቆጠረው ቅጣት ምት በድጋሚ አቻ መሆን ችለዋል። በ90+11 ፓልመር ሶስተኛዉን እና ለጨዋታው ሃትሪክ በመስራት ቼልሲ የማይታመን ሁኔታ ድል አስመዝግቧል።