በ37ኛው ዙር የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ አርሰናልን አስተናግዷል። በዚሁ አንጋፋ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ መድፈኞቹ ነበሩ የተሻለ የማሸነፍ ግምት የተሰጣቸው። ዩናይትድም እንዲሁ በውድድር አመቱ መጨረሻ ለአውሮፓ ውድድሮች የማለፍ ተስፋ ስላላቸው ሽንፈትን በጭራሽ አያስቡትም ነበር።
ጨዋታው ዘገም ያለ ነበር። በራያም ሆነ በኦናና ጎል ላይ ከአልፎ አልፎ ሙከራዎች ውጪ አስጊ እሚባል የማጥቃት ሙከራዎች አልነበሩም። ሆኖም በ20ኛው ደቂቃ ላይ ትሮሳርድ ከ ሃቨርትዝ የተላከለትን ኳስ ወደ ግብ ቀይሮ አርሰናልን ቀዳሚ አደረገ።
ሁለተኛው አጋማሽም በሜዳው እንቅስቃሴ ላይ ብዙም ለውጥ አልታየበትም። ሁለቱም ቡድኖች የግብ ዕድሎችን ተጠቅመው ተመልካቹን ማስደሰት አልቻሉም። እንግዶቹ አርሰናል ውጤት ለማስጠበቅ ነው የተጫወቱት ማለት ይቻላል። አስተናጋጆቹ ዩናይትድ የአርሰናልን የተከላካይ ክፍል ለመስበር ሲቸገሩ ነው የታዩት።
በጨዋታው መገባደጃ ላይ እንግዶቹ በዩናይትድ የጎል ክልል ጥቂት አደገኛ ሙከራዎች ለመፍጠር ችለው ነበር። ሆኖም ግን ጨዋታው ተጨማሪ ጎል ሳይታይበት 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በ አርሰናል አሸናፊነት ተጠናቋል።
ከጨዋታው መልስ ማንቸስተር ዩናይትድ በስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። አርሰናል ደሞ የሊጉ መሪነት አስጠብቋል። ማን ሲቲን በ1 ነጥብ ብቻ በመቅደም ሊጉን እየመራ ይገኛል። ሆኖም ሲቲ አሁንም በእጁ አንድ ተጨማሪ ጨዋታ ስላለው የአርሰናል ዋንጫ መብላት ጋና እርግጥ አደለም።
በመጨረሻው የፕሪሚየር ሊግ ዙር የሚኬል አርቴታ ቡድን ኤቨርተንን ይገጥማል። ቀያይ ሰይጣኖቹ ከማን ሲቲ ጋር ከሚያደርጉት የኤፍኤ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በተጨማሪ በሊጉ ሁለት ጨዋታዎች ይቀሩታል።
Premier League, 37th round
Manchester United – Arsenal – 0:1
Goal: Trossard, 20