የሪያል ማድሪድ ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪዎች በአሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ራፋኤል ቫራንን ወደ ክለቡ ለመመለስ ያላቸውን ፍላጎት በመቃወም ጣልቃ ገብተዋል። በጉዳት ምክኒያት የመሀል ተከላካይ አማራጮች እያጡ በመምጣታቸው አንቸሎቲ በጥር ወር ቫራንን ከማንቸስተር ዩናይትድ ለማምጣት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፅዋል።
በሰኔ ወር ኮንትራቱር ይሚጨርሰው ቫራን እንደገና ወደ ማድሪድ ለመመለስ ትልቅ ፍላጎት አሳይትዋል። አንቸሎቲም ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖራቸውም ንገር ግን የሪያል ማድሪድ ማኔጅመንት ተስፋውን ውድቅ አድርገውታል።
በምትኩ የሪያል ማድሪድ የተጫዋቾት ፍለጋ ኃላፊ ጁኒ ካላፋት ሌሎች ሊሆኑ የሚችሉ አማራጭ ተጫዋቾች እየተመለከቱ ነው። ነገር ግን እስካሁን ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝን ያረካ ምንም አማራጭ አልተገኘም።