ማንቸስተር ዩናይትድ በቅርቡ ባደረገው ግጥሚያ በኖቲንግሃም ፎረስት ሲቲ ግራውንድ ስታድየም 2-1 ሽንፈትን አስተናግዷል። ምንም እንኳን ከዚህ ቀደም በኖቲንግሃም ፎረስት ላይ በተከታታይ የማሸነፍ ታሪክቢኖረውም ዩናይትዶች በህመም ምክንያት ራስሙስ ሆይለንድ ባለመገኘቱ እንቅስቃሴው እንቅፋት ሆኖበታል።
ምንም እንኳን ማርከስ ራሽፎርድ በኖቲንግሃም ፎረስት የግብ ጠባቂው ማት ተርነር ስህተት ዩናይትድን የማስተዛዘኛ ጎል ቢያስቆጥርም በሁለተኛው አጋማሽ በኒኮ ዶሚኒጌዝ የተገኘው ጎል ምክንያት ኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታውን በድል አጠናቋል። ሽንፈቱ የዩናይትድ በውድድር ዘመን እየቀጠለ ያለውን ውጤት የማጣት ችግር አጉልቶ አሳይተዋል።
ማንቸስተር ዩናይትድ ዋና ዋና ተጫዋቾቹ አለመኖራቸው ውጤቶችን ለማስመዝገብ በሚያደርጉት ጥረት እንቅፋት እንደሆነ ይገለፃል። የትናቱ ዩናትድ ላይ የደረሰው ሽንፈት ቡድኑ የተሳካ የሊግ ጉዞ ለማረግ እነዚህን ችግሮች መፍታት እንደሚያስፈልግ አሳይቷል።