Inter Miami: Barcelona ቁጥር ሁለት?

ያጋሩት

የኢንተር ማያሚ ባለቤት ጆርጅ ማስ እንዳለውና ቃል በገባው መሰረት የእግር ኳስ ቡድኑ ትላልቅ የእግር ኳስ ኮከቦችን በማስፈረም ላይ ይገኛል። በስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ከሜሲ፣ ቡስኬት እና ከጆርዲ አልባ ጋር ይጫወት የነበረው ሉዊስ ሱዋሬዝ እነሱን በመከተል ቡድኑን ተቀላቅሏል። 

ክለቡ የሱዌሬዝን መምጣትን በይፋ በገለጸበት፡- “እንኳን ወደ ማያሚ ሉዊስ ሱዋሬዝ መጣህ” የሚል መልእክት አሥተላልፏል። ሱዋሬዝም በዚህ አዲስ ጅማሬ በጣም እንደተደስተ እናም ኢንተር ማያሚ ብዙ ዋንጫዎችን እንዲያሸንፍ መርዳት እንደሚፈልግም ገልጿል። 

ሱዋሬዝ የአሜሪካ የእግር ኳስ ሜጀር ሊግ እንደሚገልጸው ‘የተሰየመ ተጫዋች (designated player)’ ስም አይደለም ወደ ኢንተር ማያሚ የተቀላቀለው ፣ ይህም ማለት ደመወዙ በአሜሪካ የእግር ኳስ ሜጀር ሊግ(MLS) ከተቀመጠው ገደብ በላይ አያልፍም። እንደ ቲዬሪ ሄንሪ እና ዴቪድ ቤካም በቅርቡም የገባው ሊዮለን ሜሲ ያሉ ታዋቂ ተጫዋቾች (designated player) ከዚህ በፊት ተጨዋቾች ተብለው ተለይተዋል። የሱዋሬዝ ክፍያው በግልፅ መረጃ ባይወጣም፣ እንደ መነሻ ደሞዝ 1.7 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ሊያገኝ እንደሚችል ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፣ ይህም ቦነሶች ጨምሮ በዓመት እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር የማገኝበት ዕድል አለው።

ያጋሩት