ግብፅ የመጀመርያው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ሞሃመድ ሳላህ ከሞዛምቢክ ጋር 2-2 በሆነ አቻ ውጤት እንዲጠናቀቅ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ግብፅ በሞስታፋ መሀመድ ጎል ቀዳሚ ብትሆንም ሞዛምቢክ በሁለተኛው አጋማሽ በዊቲ እና ክሌሲዮ ጎሎች ጨዋታውን ቀይራለች። ነገርግን ግብፅ በአቻ ውጤት እራሱዋን ማዳን ችላለች፣ VAR ሳላህ ላይ ፋውል መሰራቱን ካረጋገጠ ቡኋል ሳላህ በፍፁም ሰአት ቅጣት ኳሱን ከ መረብ አገናኝቶ ጨዋታውን 2-2 በሆነ ውጠት አጠናቀዋል።
ጨዋታው የጀመረው ግብፅ በፍጥነት በመሪነት በመምራት ሳላህ የመታው ኳስ ለሞስታፋ መሀመድ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖ በማስቆጠር ነበር። ግብፅ መሪነቱን ለማራዘም ዕድሎችን ብታገኝም ሞዛምቢክ በመታገል በ55ኛው ደቂቃ የተዋጣውን ኳስ ዊቲ በግንባሩ በማስቆጠር እና ክሊሲኦ ከሶስት ደቂቃዎች በኋላ በማስቆጠር መሪነቱን ወስደዋል። ግብፅ አቻ ለመሆን ሞክራለች እና ጥረታቸው በጭማሪ ሰአት ሳላህ ከፍፁም ቅጣት ምት አግኝቶ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት በአስደናቂ ሁኔታ መጠናቀቁን አረጋግጧል።