የሰሞኑን የዝውውር ወሬዎች

ያጋሩት

የክሪስታል ፓላሱን የክንፍ መስመር ተጫዋች ማይክል ኦሊሴን ለማስፈረም ሊቨርፑል ቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድን ተቀላቅሏል። ማንቸስተር ዩናይትድ የባርሴሎናውን ተከላካይ ጁልስ ኩንዴ ለማዘዋወር €40m የዝውውር ዋጋ እያዘጋጀ ይገኛል። በሌላ በኩል ላዚዮ የዩናይትዱን አጥቂ ሜሰን ግሪንዉድን በ£30m ለማስፈረም እየተነጋገረ ነው።

ባየር ሙኒክ የፒኤስጂውን አማካይ ዣቪ ሲሞንስን ኢላማ አድርጓል ነገርግን ስምምነቱ ወደ €100m ሊፈጅ ይችላል። ቼልሲዎች ለቦካ ጁኒየርስ ወጣት የመሀል ተከላካይ አሮን አንሴልሚኖ 13 ሚሊየን ፓውንድ አቅርበዋል። በተጨማሪም ማንቸስተር ሲቲ የኤደርሰን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ እርግጠኛ ባለመሆኑ የሰንደርላንድ ግብ ጠባቂ አንቶኒ ፓተርሰንን ይፈልጋሉ።

አርሰናል የሪያል ሶሲዳዱን ማርቲን ዙቢሜንዲ ለማስፈረም ከተቸገረ በኋላ የኒውካስልሱን ብሩኖ ጉይማራሬስን እያሳደደ ይገኛል ነገርግን የስፖርቲንግ ሲፒውን ቪክቶር ጂዮከርስ የውል ማፍረሻውን አያሟላም። ቶተንሃም እና ማንቸስተር ዩናይትድ የሊሉን አጥቂ ጆናታን ዴቪድን ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ሪያል ማድሪድ ተከላካይ ራፋ ማሪንን ለናፖሊ ለመሸጥ በኋላ ለመግዛት በሚል ውል እየተደራደረ ነው። ዌስትሃም በአል ኢቲሃድ ኢላማ የሆነውን መሀመድ ኩዱስን ለማቆየት ፈተና ገጥሞታል።

ያጋሩት