የሰሞኑን የዝውውር ወሬዎች

ያጋሩት

ማንቸስተር ዩናይትዶች የሪያል ማድሪዱን ሮድሪጎ ለማስፈረም ትልቅ የ120 ሚሊየን ዩሮ ክፍያ ለማቅረብ ይፈልጋሉ። ሪያል ማድሪድ ኬሊያን ምባፔን ካገኘ በኋላ ሊለቀው ይችላል ብለው ስላሰቡ እሱን ይፈልጋሉ። እንደ ሪያል ማድሪድ፣ ባርሴሎና እና ቼልሲ ያሉ ትልልቅ ክለቦችን ቀልብ የሳበው እስቴቫኦ የተባለ የፓልሜራስ ወጣት ተጫዋች ንግግርም አለ።

ቼልሲዎች አጥቂያቸውን ሮሜሉ ሉካኩን ለመሸጥ ከሳውዲ አረቢያ ኤፍኤ ጋር እየተነጋገሩ ነው። ለእሱ ወደ 60 ሚሊዮን ዩሮ ይፈልጋሉ ነገር ግን ትንሽ ገንዘብ መቀበል አለባቸው። በሌላ በኩል ቶተንሃም ሆትስፐር የ21 አመቱን የቦሎኛ የመሀል ተከላካይ ሪካርዶ ካላፊዮሪን የማስፈረም ፍላጎት አለው።

ዣቪ አሎንሶ በባየር ሊቨርኩሰን መቆየቱ ፍሎሪያን ዊርትዝ ወደ ማንቸስተር ሲቲ ወይም ሊቨርፑል አለመሄዱን አረጋግጧል። ሪያል ማድሪድ ለወደፊት ዝውውራቸውን ሲያቅዱ የሊቨርክሰኑን ዊርትዝን እየተከታተሉ ይገኛሉ። እንዲሁም ማንቸስተር ዩናይትዶች የናፖሊውን የቀኝ መስመር ተከላካይ ጆቫኒ ዲ ሎሬንዞ ለማስፈረም ፍላጎት ያላቸው ሲሆን ቼልሲዎች ደግሞ የሪያል ማድሪዱን አማካኝ አውሬሊን ቹአሜን ለማስፈረም እያሰቡ ነው።

ኒውካስል ዩናይትድ አማካዩን ብሩኖ ጉይማራስን በፋይናንሺያል ህግ ምክያት መሸጥ ይኖርበታል። እንደ አርሰናል፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ፒኤስጂ ያሉ ትልልቅ ክለቦች እሱን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። በሌላ በኩል የቦሎኛ አጥቂ ጆሹዋ ዚርክዚ ከማንቸስተር ዩናይትድ፣ አርሰናል እና ጁቬንቱስ የቀረበለትን ጥያቄ ቢያቀርብም ወደ ኤሲ ሚላን ሊቀላቀል ነው። በመጨረሻም ሌስተር ሲቲ የአርሰናሉን ኢዲ ንኪቲያህን ለማስፈረም እየተጠባበቀ ሲሆን ከብሬንትፎርድ እና ክሪስታል ፓላስንም ትኩረት እየሳበ ይገኛል።

ያጋሩት