የሰሞኑን የዝውውር ወሬዎች

ያጋሩት

ማንቸስተር ዩናይትዶች እንደ ማርክ ጉሂ እና ማቲሃስ ዴ ሊጊት ያሉ ተጫዋቾችን ግምት ውስጥ በማስገባት ከኤቨርተኑ ጃራድ ብራንትዋይት ጋር በተገናኘ ከዋጋው ውድነት የተነሳ አማራጮችን ይፈልጋሉ። ባርሴሎና የዩናይትዱን ወጣት ኮቢ ማይኖን ይፈልጋል፤ ቼልሲዎች ከአስቶንቪላው ጆን ዱራን ጋር እየተነጋገሩ ነው።

አርሰናል ኤሚል ስሚዝ ሮዌን በ30 ሚሊየን ፓውንድ ለመሸጥ ተዘጋጅቷል እና የኤቨርተኑን አማዱ ኦናናን ጠይቀዋል እሱም 50 ሚሊየን ያወጣል። ቶተንሃም የክሪስታል ፓላስን ኢቤሬቺ ኢዜን ይፈልጋሉ እና የውል ማፍረሻውን £60m ለመክፈል ተዘጋጅተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባየር ሙኒክ የፉልሃሙን ጆአኦ ፓልሂንሃ ማሳደዱን ቀጥሏል ፉልሃም በምትኩ ካልቪን ፊሊፕስን እየተመለከተ ይገኛል።

ሪያል ማድሪድ ከካፒቴን ናቾ ፈርናንዴዝ ጋር ወደ አል ኢቲሃድ ለመዘዋወር እየተደራደረ ሲሆን የኤስፓኞል ሆአን ጋርሲያ የመጠባበቂያ ግብ ጠባቂ ምርጫ አድርጎ አስቀምጧል። ሊቨርፑል ቨርጂል ቫንዳይክ ከሳውዲ አረቢያ ፍላጎት ቢኖረውም አዲስ ኮንትራት እንዲፈራረም ሲጠብቅ የባርሴሎናው ካፒቴን ሰርጊ ሮቤርቶ ከበርካታ የላሊጋ ክለቦች ፍላጎትን ስቧል።

ያጋሩት