የሰሞኑን የዝውውር ወሬዎች

ያጋሩት

ጁቬንቱሶች ከማንቸስተር ዩናይትድ ጃዶን ሳንቾን የማስፈረም ፍላጎት አላቸው፤ ተጫዋቹን ሳያተርፉ ሊሸጡት ይችላሉ። ጁቬንቱሶችም ከአስቶንቪላው ዳግላስ ሉዊዝ የተጫዋቾች ቅያሬዎችን ከዌስተን ማኬኒ እና ሳሙኤል ኢሊንግ-ጁኒየር ጋር በ17m አቅርበዋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ ለጃራድ ብራንትዋይት የኤቨርተንን £70m ዋጋ ለመክፈል ቢያቅማሙም ሰር ጂም ራትክሊፍ ስምምነቱን እንደሚያገኝ እርግጠኛ ናቸው። ቼልሲዎች ቤንጃሚን ሴስኮን ማስፈረም ባለመቻላቸው የአስቶንቪላውን አጥቂ ጆን ዱራን ለማስፈረም አቅደዋል። በተጨማሪም ቼልሲ፣ ማን ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐር የፖርቶ አጥቂ ኢቫኒልሰን የውል ማፍረሻውን £85m ቢሆንም እያጤኑት ነው።

ባየር ሙኒክ በአዲሱ አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ የሚመራውን የሊቨርፑሉን ጆ ጎሜዝ ፍላጎት አሳይቷል። የሪያል ማድሪዱ አንቶኒዮ ሩዲገር ከሳዑዲ አረቢያው አል ናስር የ100ሚ.ዩሮ ጥያቄ ሚመጣለትም እሱ ግን መቆየት ይፈልጋል። በሌላ በኩል የሪያል ማድሪዱ አንድሪ ሉኒን ወደ አርሰናል ለመዘዋወር እያሰበ ሲሆን ባርሴሎና ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በጆአዎ ካንሴሎ ላይ እየተደራደረ ይገኛል።

ያጋሩት