የሰማያዊ ካርድ ቅጣት ለእግር ኳስ ተጫዋቾች

ያጋሩት

የአለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፊፋ (FIFA) የሰማያዊ ካርድ ቅጣት ወይም አስር ደቂቃ ከጭዋታ እገዳ ሕግ በትላልቅ የእግርኳስ ውድድሮች እንደ ማይጀመር ገለፀ።

ከ1970 ዓ.ም ጀምሮ በእግር ኳስ የካርድ ቅጣት አሰጣት እና ህጎች ተመሳሳይ ናቸው ፣ ቢጫ ማስጠንቀቅያ ለመስጠት ሲሆን ቀይ ደሞ ተጫዋቹ ከጭዋታው ለማባረር ነው። በቅርብ ግዜያት የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት የካርድ ቅጣቶች አሰጣት ላይ ለውጥ እንደሚደረግ ነው። በዚህ አሰራር ምንም እንኳን የቅርብ ጊዜ ሪፖርቶች ለወደፊቱ ሊለወጡ እንደሚችሉ ጠቁመዋል ።

የአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ቦርድ (IFAB) አጥፊ ተጫዋቾችን ለ10 ደቂቃ ያህል ወደ የቅጣት ክፍል (sin bin) በመላክ ያልተፈለጉ የተጫዋች ባህሪን ለመግታት አስቧል። ይህም የሚሆነው አንድ ተጫዋች ከቢጫ ከፍ ያለ ግን ደሞ ቀይ የማያሰጥ ጥፋት ከሰራ በሰማያዊ ካርድ ከሜዳው ወጥቶ ወደ ቅጣት ክፍል(sin bin) እንዲገባ ይደረጋል። አስር ደቂቃ ከቆየ በኋላም ወደ ጭዋታ ይመለሳል።

ይህ አሰራር ቀደም ብሎም ዝቅተኛ ደረጃ ባሉ ውድድሮች ላይ እየተተገበረ ቢሆንም ፊፋ አርብ ፌብሩዋሪ 9 2024 ባወጣው መግለጫ ይህ ስርዓት በቅርብ ጊዜ ወደ ከፍተኛ የእግር ኳስ ውድድሮች (ሊጎች) እንደማይመጣ ግልጽ አድርጓል።ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ስፖርት ባይብል እንደዘገበው የእግር ኳስ ማህበሩ የሰማያዊ ካርዶች የመጀመሪያ ደረጃ ሙከራ ስኬታማ ከሆነ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን የኤፍኤ ዋንጫ (FA CUP) ውድድሮችን ለሙከራ ለማቅረብ እያሰበ ነው።

የቅጣት ክፍሎች (sin bin) በተለምዶ እንደነ ራግቢ አይስ ሆኪ በመሳሰሉ ስፖርቶች ውስጥ ጥቅም ላይ እየዋሉ ናቸው።

ያጋሩት