ማንቸስተር ዩናይትድ የጂሮናን ኮከብ የግራ መስመር ተከላካይ ሚጌል ጉቲሬዝን ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ ገብተዋል። የ22 አመቱ ወጣት እስካሁን በላሊጋው የውድድር ዘመን እጅግ አስደናቂ ነው። ጂሮና ሊጉን ከሚመሩት አጠገብ እንደተቀመጠ ጉቲሬዝ እራሱን በዝውውር መስኮቱ ውስጥ እያስቀመጠ ነው።
እንደ The Sun, ዩናይትድ ባለፉት ሳምንታት የግራ መስመር ተከላካዩን ለመመልከት ስካውት በመላክ ላይ ይገኛሉ። የእግር ኳስ አዋቂነቱ እና አጠቃላይ አጨዋወቱ ዩናይትድን በእጅጉ አስደምሟል። የክረምቱ ዝውውር የማይመስል ቢሆንም ዩናይትዶች በክረምቱ ዝውውር ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል።