የ38 አመቱ የአል ናስር አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ(CR7) በግሎብ እግር ኳስ ሽልማት ስነስርአት ላይ ስለ ዘንድሮው ሻምፒዮንስ ሊግ ግምቱን ገልጿል። የአመቱን የደጋፊዎች ምርጥ ተጫዋች ፣የምርጥ ግብ አስቆጣሪ እና የመካከለኛው ምስራቅ ምርጥ ተጫዋች ሽልማቶችን የተቀበለው ሮናልዶ ማንቸስተር ሲቲ ፣ ባየር ሙኒክ ወይም ሪያል ማድሪድ ሻምፒዮን ሆነው እንደሚወጡ ያምናል። የማንቸስተር ሲቲውን የአጨዋወት ዘይቤ ያደነቀው ሮናልዶ የማሸነፍ እድል እንዳላቸው ሰፊ እንደሆነ ይገልፃል። እነዚህ ሶስት ክለቦች ቻምፒዮንስ ሊጉን የመብላት የተሻለ እድል አንዳላቸው ነው የአልናስሩ ኮከብ የትናገረው።
ሮናልዶ በ2023 ባሳየው ድንቅ ብቃት ለአል ናስር እና ለፖርቹጋል 54 ጎሎችን በማስቆጠር የምርጥ ግብ አስቆጣሪ ሽልማት ተሸልሟል። ወደ 39 አመቱ ቢጠጋም እንደ ሃሪ ኬን፣ ኪሊያን ምባፔ እና ኤርሊንግ ሃላንድ ካሉ ወጣት ተጫዋቾች በልጦ ተገኝቷል። ሮናልዶ ተጠራጣሪዎችን የተሳሳቱ መሆናቸውን በማሳየት ኩራት ይሰማዋል ትችትን የመቋቋም ችሎታ አፅንዖት ይሰጣል።
በአሁኑ ሰአት የሮናልዶ ቡድን አል ናስር በሳዑዲ ፕሮ ሊግ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ መሪውን አል ሂላል በሰባት ነጥብ ይከተላል። የአል ሂላል ቡድን እንደ ሩበን ኔቭስ፣ ሰርጌጅ ሚሊንኮቪች-ሳቪች፣ ማልኮም፣ አሌክሳንደር ሚትሮቪች፣ ሬናን ሎዲ፣ ካሊዱ ኩሊባሊ፣ ቦኖ እና የተጎዳው ኔይማር ያሉ ታዋቂ ተጫዋቾችን ያካትታል።