በዌስትሃም ዩናይትድ እና አርሰናል መካከል በተካሄደው ጨዋታ ዌስትሃም መጠነኛ አለመግባባቶችን በፈጠረ መልኩ መሪነቱን ወስዷል። ቶማስ ሶውኬክ በ13ኛው ደቂቃ ከጃሮድ ቦወን የተቀበለውን ኳስ ጎል አስቆጥሯል። ግቡ ኳሱ ከጨዋታ ውጪ መሆን ወይ አለመሆኑን ለመፈተሽ በ VAR ለሶስት ደቂቃ ተኩል የተገመገመ ቢሆንም ከታዩት የካሜራ ቅጅዎች መካከል አንዳቸውም በግልፅ ሊያሳዩት አልቻሉም። እርግጠኛ ባይሆኑም ዳኛዎቹ በመጀመሪያ ውሳኔያቸው ፀንተው ግቡን አጸደቁ። በዘንድሮው የውድድር አመት አርሰናል ለሁለተኛ ጊዜ ነው በአከራከሪ የ VAR ግምገማን ተከትሎ ጎል ያስተናገደው።
“እኛ ባለን ቴክኖሎጂ ወጣ ወይም ገባ ማለት አለመቻላችን አና ያን ያህል ግልጽ አለመሆኑ አሳፋሪ ነው” አሰልጣኝ አርቴታ
አርሰናል 2-0 ሽንፈት ያስተናገደበት ጨዋታ የነበረ ሲሆን የቀድሞ የመድፈኞቹ ተከላካይ ኮንስታንቲኖስ ማቭሮፓኖስ ከጀምስ ዋርድ-ፕሮውስ የማእዘን ምት በግንባሩ መትቶ ሁለተኛዋን ግብ አስቆጥሯል። በመጨረሻው ሰዓት ዌስትሃም 3-0 የመውጣት እድል በፔናሊቲ ቢያገኝም የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ አድኖታል። ይህ ሽንፈት በዚህ የውድድር ዘመን ለአርሰናል ፈተናዎችን የጨመረ ሲሆን ጨዋታው አወዛጋቢ በሆነው የ VAR ውሳኔ እና ማቭሮፓኖስ ለዌስትሃም ድል ላበረከተው አስተዋፅዖ የጎላ ነበር።