የአርሰናል የዋንጫ ጉዞ በአስቶንቪላ ተደናቀፈ

ያጋሩት

በ33ኛው ዙር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች አርሰናል በሜዳው በአስቶንቪላ ሽንፈት አስተናግዷል። ይህ ሽንፈት የዋንጫ ተስፋው ላይ ከባድ ጉዳትም ጥሏል።

የመጀመርያው አጋማሽ በባለ ሜዳዎቹ አርሰናል መጠነኛ ብልጫ የታየበት ቢሆንም ሁለቱም ቡድኖች 0-0 በሆነ ውጤት ወደ እረፍት ገብተዋል። የለውጡ ነጥብ የተገኘው በጨዋታው መገባደጃ ደቂቃ ላይ ነው። በመጀመሪያ ሊዮን ቤይሊ ከሉክ ዲግ የተቀበለውን ኳስ ተጠቅሞ ባዶ መረብ ውስጥ ግብ ያስገባ ሲሆን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ኦሊ ዋትኪንስ ከግብ ጠባቂውጋ አንድ ለአንድ ተፋጥጦ ሁለተኛውን ጎል በማስገባት የኢምሬትስ ስታዲየምን አስደንግጧል።

አርሰናል የጭዋታ የበላይነት ቢኖረውም ለድል ግን አልበቃውም። በተቃራኒው አስቶንቪላ በሁለት ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች ብቻ 2 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። ከዚህ የሽንፈት ጨዋታ በኋላም የአርቴታ ልጆች ማንቸስተር ሲቲን በሁለት ነጥብ በመከተል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። መድፈኞቹ ከቼልሲ፣ ቶተንሃም እና ማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በሚደረጉ ጨዋታዎች ገና ከባድ ቀሪ ፊልሚያዎች እንደሚጠብቃቸው ግልፅ ነው።

33ኛው ዙር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ
Arsenal vs Aston Villa – 0:2
Goals: Bailey 84, Watkins 87.


ያጋሩት