Vitor Roque ወደ Barcenola ከመሄዱ በፊት የላከው መልእክት

ያጋሩት

ባርሴሎና የ18 አመቱን አጥቂ በክረምቱ ለማስፈረም እስከ £52m የሚደርስ ስምምነት የተደረሰ ሲሆን ያለፉትን ስድስት ወራት ከላሊጋው የፋይናንሺያል ፌር ፕሌይ ህግጋት ጋር በመስራት ሮክን በ January ወር በይፋ መመዝገብ ይችል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ውዲያውኑ ለሮክ ፊርማ ጊዜ ካገኙለት በኋላ ሮክ በቪዲዮ ራሱ መምጣቱን ከማግለጹ በፊት ባርሴሎና በማህበራዊ ድህረ ገጻቸው ላይ የሮክን መምጣት ቀድመው ገለጹ።

በማክሰኞ እለት ለባርሴሎና ደጋፊዎች “ኩለርስ በቅርቡ እንገናኝ” አለ።

ሮክ በእለቱ አውሮፕላን ማረፊያ ደረሰ። እና ረቡዕ ማለዳ ላይ በሚያርፍ በረራ ሊሳፈር ተዘጋጅቷል።

ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ሮክ አርብ ከአዲሱ አሰልጣኝ ዣቪ ጋር እና ከባርሴሎና ተጫዋቾች ጋር ለስልጠና ከመግባቱ በፊት በስፔን ካለው ኑሮ ጋር ለመላመድ የሁለት ቀናት ጊዜ እንደሚሰጠው ገልጸዋል።

“ለቡድኑ ተስፋ ነው” ሲል ዣቪ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ለሮክ ተናግሯል። “እሱ በጣም ጥሩ አዲስ ፈራሚ ትጫዋች ነው እና ለእኛ ብዙ አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይችላል ብዬ አስባለሁ። ብዙ አዎንታዊ ነገሮች ወደ አእምሮዬ ይመጣሉ, እና ስለ አማራጭ ለማሰብ ጊዜ የለኝም። ስራ፣ ግቦች፣ መስዋዕትነት … እሱ ያ ተጫዋች ነው”።

“በቪቶር ሮክ ላይ ወይም እንደ ላሚን ያማል ያሉ ወጣቶች ላይ ጫና መፍጠር አንችልም። ደረጃ በደረጃ መሄድ አለባቸው። በቡድን አንድ እርምጃ ወደፊት መሄድ አለብን። ለውጥም ማምጣት አለብን፣ በእነዚህ ቦታዎች ላይ ውጤታማነት ይጎድለናል። ውጤታማ አልመሆናችን በብዙ ጨዋታዎች ላይ ዋጋ አስከፍለውናል። በላሊጋ ውስጥ ነገሮችን መለወጥ ከፈለግን እዚያ ቦታ ላይ ማሻሻል አለብን”።

ሮክ በዚህ የውድድር ዘመን ከጎል ፊት ለፊት ካለው ከፍ ያለ ደረጃውን ማዛመድ ያልቻለውን ከደጋፊዎች ከፍተኛ ትችት ለገጠመው የ35 አመቱ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ አፋጣኝ ፉክክር ያማጣል።

ያጋሩት