Barcelona ወደ ፍፃሜ አለፈ

ያጋሩት

በሱፐርኮፓ ዴ ኢስፓኛ ባርሴሎና ኦሳሱናን 2-0 አሸንፏል ነገር ግን ጨዋታው ብዙም አስደሳች ተብሎ ሚታሰብ አልነበረም። ባርሴኖላ ሲቸገር ነው የታየው። ሮበርት ሌዋንዶውስኪ እና ላሚን ያማል ለባርሳ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። ባርሴኖላ ዋንጫ መብላት ከፈለገ ከሪያል ማድሪድ ጋር በሚኖረው የፍጻሜው ጨዋታ የተሻለ አቋም ማሳየት ይጠበቅበታል።

በሪያል ማድሪድ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ከነበረው ጨዋታ ሲነፃፀር የጎል ብዛት  ያነሰ እናም ቀርፈፍ ያለ ጨዋታ ነው የነበረው። ባርሴሎና ጥቂት ሙከራዎችን አድርጓል፣ ነገር ግን ኦሳሱና ጎል የማግባት ብዙ አጋጣሚዎች ፈጥሮ ነበር ። የመጀመሪያው ግልፅ እድል የተገኘው በ38ኛው ደቂቃ ላይ አንቴ ቡዲሚር የሞከረውን ኳስ የባርሴሎና ግብ ጠባቂ ኢናኪ ፔኛ አድኖታል።

ላሚን ያማል ተቀይሮ በገባ ጊዜ ባርሴሎና ትንሽ ተሻሽሎ ነበር። ወሳኙ የመጀመርያ ግብ ኢልካ ጉንዶጋን ባመቻቸው ኳስ ሌዋንዶውስኪ አስቆጠረ። ሌዋንዶውስኪ ሁለተኛው ጎሉ ለማግባት ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም የኦሳሱና ግብ ተባቂው ጂሰስ አሬሶ ሙከራው አስቆመው።

በመጨረሻው ደቂቃዎች ጆአዎ ፌሊክስ ባረገው ብልህ አጨዋወት ለያማልን ግብ የሞሆን ኳስ አመቻቸለት ያማልም የትረጋጋ አጨራረስ በማረግ ሁለተኛው ጎል አስቆጠረ። ባርሴሎና ከሪያል ማድሪድ ጋር በሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ የተሻለ አቋም ማሳየት ግድ ይሆንበታል።


ያጋሩት