በ Euro 2024 England እና Denmark በአቻ ውጤት ተለያሉ

ያጋሩት

እንግሊዝ ከዴንማርክ ጋር በዩሮ 2024 ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት በመለያየቷ ወደ ጥሎ ማለፍ የማለፏን ነገር አዘግይቶታል። ለእንግሊዝ ሃሪ ኬን ቀደም ብሎ ጎል አስቆጥሯል ነገርግን ዴንማርክ በሞርተን ሆይሉማንድ ጎል አቻ መሆን ችላለች። ምድብ ሶስትን በአራት ነጥብ ብትመራም የእንግሊዝ እንቅስቃሴ ደካማ ነበር እና ዴንማርክ ጠንካራ አጨዋወት በማሳየቷ እንግሊዝ ከስሎቬንያ ጋር የምታደርገውን ቀጣይ ግጥሚያ ለማሻሻል መጣር ይኖርባታል።

ጨዋታው በሁለቱም ቡድኖች ስህተት የጀመረ ሲሆን ኬን በ18ኛው ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥሮ በእንግሊዝ ታላላቅ የውድድር መድረኮች የጎል ሪከርዱን አስመዝግቧል። ዴንማርክ ግን አቻ የሚያደርጋቸው ጎል በሆይሉማንድ ከ30 ሜትሮች ርቀት አስቆጥሯል። ዴንማርካውያን በአጠቃላይ የተሻለ ተጫውተዋል፤ ፒየር ኤሚል ሆይብይርግ የጨዋታው ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ቢመረጥም ባለማሸነፉ የተሰማውን ብስጭት ገልጿል።

ጋሬዝ ሳውዝጌት በመጨረሻዎቹ 20 ደቂቃዎች ውስጥ እንደ ኬን እና ሳካ ያሉ ቁልፍ ተጫዋቾችን ቀይሮ ቡድኑን ለማደስ ቢሞክርም ሁለቱ ቡድኖች ግን በርካታ የጎል እድሎችን አምክነዋል። ሰርቢያን ባሸነፈበት የመክፈቻ ጨዋታ ላይ ያደመቀው እንግሊዛዊው ጁድ ቤሊንግሃም ከዴንማርክ ጠንካራ የአማካይ ክፍል ጋር ትግል ውጥ ገብቶ ነበር። እንግሊዝ ከ ስሎቬንያ ጋር የምታደርገው ቀጣይ ጨዋታ ለእድገቷ ወሳኝ ሲሆን ዴንማርክ ደግሞ ሰርቢያን ትገጥማለች ሁሉም ቡድኖች አሁንም ፉክክር ላይ ናቸው።

ያጋሩት