በ Algeria እና በ Burkina Faso መሀል የነበረው ትንቅንቅ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

ያጋሩት

በአፍሪካ ዋንጫ አልጄሪያ እና ቡርኪናፋሶ የሁለተኛው ዙር ጨዋታ አድርገዋል። በጨዋታው የመጀመርያው አጋማሽ ብዙ የጎል እድሎች ባይታዩም የቡርኪናፋሶው አህመድ መሀመድ ኮናቴ ከእረፍት በፊት ጎል አስቆጥሯል። ከቫር (VAR) ግምገማ በኋላ ግቡ ተረጋግጧል።

በሁለተኛው አጋማሽ አልጄሪያዊው ባግዳድ ቦውንድጃህ ጎል አስቆጥሮ ቡድኑን አቻ አድርጓል። በመቀጠል ቡርኪናፋሶ የፍፁም ቅጣት ምት አግኝታ በርትራንድ ትራኦሬ ኳሱን ከመረብ አገናኝቷል። ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሲል ለአልጄሪያ አስጨናቂ ግዜ ሆኖቧቸው ነበር ነገርግን ቡነጃህ በመጨረሻ ሰአት በድጋሚ አስቆጥሮ ቡድኖቹ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።

በመጨረቻም ቡርኪናፋሶ በውድድሩ አራት ነጥብ ስትይዝ አልጄሪያ ደግሞ ሁለት ነጥብ አያት እና ወደ ጥሎ ማለፍ ላትገባ ይምትችልበት ግምት ስላለ ስጋት ውስጥ ነች።


ያጋሩት