ሴኔጋል ካሜሩንን 3-1 በማሸነፍ በአፍሪካ ዋንጫ(AFCON) ወደ ጥሎ ማለፍ ውድድር ማለፉን አረጋግጣለች። ኢስማኢላ ሳር በመጀመርያው አጋማሽ ጎል አስቆጥሯል። ሴኔጋል በትዕግስት የጠበቀችውን ሁለተኛዋን ጎል ከመጨረሻው 20 ደቂቃ ሲቀረው ሀቢብ ዲያሎ ከሳርር የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ አስቆጥሯል።
ካሜሩንን የመጀመሪያ ኢላማ የመታው ኳስ በ83ኛው ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥራ ጭዋታው ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ውጥረት የያዘ ብታረግም ሴኔጋል የተሻለ አቋሟን በመቀጠል ካሜሩን በጭማሪ ሰአት ያገኘችው አቻ የመሆን እድል ቀልብሳ ሶስተኛው ጎል በሳዲዮ ማኔ አስገብታለች። ለሶስተኛው ግብ ሞቆጠር ፓፔ ጉዬ ለስዲዮ ማኔ ያመቻቸው ኳስ ትልቅ አስተዋጾ ነበረው። #AFCON2024 #ሴኔጋል(Senegal) አሸነፈች
ሴኔጋል (Senegal) – ካሜሮን (Cameroon) – 3:1