Sancho በውሰት ወደ Dortmund ተመለሰ

ያጋሩት

ጃዶን ሳንቾ ከማንቸስተር ዩናይትድ በውሰት ወደ ቦርሲያ ዶርትሙንድ ተመልሷል እናም ውሰቱ ለቀረው የውድድር አመቱ ብቻ ነው። ዶርትሙንድ አብዛኛውን ደሞዙን ለዚህ ጊዜ የሚሸፍን ሲሆን ስምምነቱ €3.5m ነው እናም በተጨማሪ እስከ 4ሚ.ዩሮ የሚደርስ ተጨማሪ ክፍያ ሊደርስ ይችላል እሱም የሚሆነው እንደ የተጫወተው ጨዋታዎች ብዛት እና ዶርትሙንድ በቻምፒየንስ ሊግ ስኬት ያገኘ ነው። ዶርትሙንድ በውሰቱ መጨረሻ ሳንቾን ለመግዛት ምንም አማራጭ የላቸውም።

በማንቸስተር ዩናይትድ ላለፉት አራት ወራት ብዙም ተቀባይነት አጥቶ ያልነበረው ሳንቾ ከ18 አመት በታች ልጆች ጋር ልምምድ ሲሰራ ነበር። በ September ወር ላይ ከጨዋታ ውጪ ማናጀሩ የሰጡትን ማብራሪያ በመቃወም በማህበራዊ ሚዲያ ድህረ ገጽ ከአሰልጣኙ ኤሪክ ቴን ሃግ ጋር ፍጥጫ ነበራቸው። ይህም ሆኖ ዶርትሙንድ ሳንቾን በድጋሚ ሊቀበል ፍቃደኛ እና የክንፍ ተጫዋቹ በመጀመሪ ከመሸጡ በፌት በ137 ጨዋታዎች 50 ጎሎችን ያስቆጠረበት ቡድን ጋር ህይወቱን ለማደስ ጓጉቷል።

እ.ኤ.አ. በ2021 ማንቸስተር ዩናይትድን በ73 ሚሊየን ፓውንድ የተቀላቀለው የ23 አመቱ የክንፍ ተጫዋች በደስታ ለማጫወት እና ለቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ለዶርትሙንድ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ እየጠበቀ ነው። ሳንቾ ወደ ቡንደስሊጋ መመለሱ በማንቸስተር ዩናይትድ ቆይታው ከአስቸጋሪ ጊዜ በኋላ ጥሩ ብቃቱን እንዲያሳይ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ታይቷል። የዶርትሙንድ የስፖርት ዳይሬክተር ሴባስቲያን ኬህል ምንም እንኳን በቅርብ ወራት ውስጥ ሳንቾ ምንም ተፎካካሪነት ያለው ጨዋታ ባይጫወትም በፍጥነት ተመልሶ ቡድኑን በውድድር ዘመኑ ግብ እንደሚያስቆጥር እና ላማስቆጠር እድል እንደሚሰጥ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የጄደን ሳንቾ ዶርትመንድ ከገባ ቡኋል የመጀመሪው ቃለ መጠይቅ

ያጋሩት