Las Palmas 1 – 2 Barcelona

ያጋሩት

ባርሴሎና ከሊጉ እረፍት በኋላ ያደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ላስ ፓልማስን ገጥሟል። ባርሴሎና እራሱን ለማሳየት ወሳኝ ግጥሚያ ነበር። ጨዋታው በባርሴሎና እንደ ኢናኪ ፔና፣ ሮናልድ አራውሆ፣ ጁልስ ኩንዴ፣ ጆአዎ ካንሴሎ፣ አሌሃንድሮ ባልዴ፣ ኢካይ ጉንዶጋን፣ ፍሬንኪ ዴ ጆንግ፣ ሰርጂ ሮቤርቶ፣ ፌራን ቶሬስ፣ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ እና ራፊንሃ ባሉ ቋሚ ተጨዋቾች ጀመረዋል።

ባርሴሎና ኳሱን በመቆጠር እና ላስ ፓልማስን በማጥቃት ጥሩ እንቅስቃሴ አሳይተው ነበር። ሆኖም ግን ከካንሴሎ ጉዳት በሃላ ብዙም ሳይቆዩ ላስ ፓልማሶች ግብ አስቆጥረዋል። ባርሴሎናዎች የተለያዩ ታክቲኮችን ቢሞክሩም ጥሩ የጎል እድሎችን ለመፍጠር ተቸግረው ነበር። ላስ ፓልማስ በድጋሚ የጎል እድሎችን አግኝቶው ሊጠቀሙበት አልቻሉም ለባርሴሎና አስቸጋሪ እንዲሆን አድርጎታል። ነገርግን ጨዋታው በእረፍት 1-0 በመቆየቱ ለዛቪ እፎይታ ቢሰጥም ባርሴሎና ግን ጥሩ እየተጫወቱ አልነበረም።

ሁለተኛው አጋማሽ ባርሴሎና ጥሩ እንቅስቃሴ ማሳየት ጀምረው ነበር በዛም ምክንያት ፌራን ቶሬስ ግብ አስቆጥሮ አቻ መሆን ችለዋል። ባርሴሎና የጎል እድሎችን በመፍጠር የተሻለ ተጫውቷል ነገርግን ጎል ማስቆጠር አልቻሉም። ሁለቱም ቡድኖች አዳዲስ ተጫዋቾችን ቀይረው ነበር ነገርግን እስከ ጨዋታው መገባደጃ ድረስ የማሸነፊያ ጎል ማግኘት አልቻሉም።

በ90ኛው ደቂቃ ላስ ፓልማስ የፍፁም ቅጣት ምት የሰጠ ሲሆን የባርሴሎናው ኢካይ ጉንዶጋን አስቆጥሮ ባርሴሎናን አስደናቂ ድል አስመዝግቧል። ባርሴሎና የቻለውን ባያደርግም በሊጉ ከሌሎች ቡድኖች ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በመቀነስ ማሸነፍ ችሏል። ሁለተኛው አጋማሽ ለባርሴሎና በጣም የተሸለ ስለነበረም በጨዋታው ሶስት ነጥብ ይዞ ጨርሷለ።


ያጋሩት