ለ 4ኛ ጊዜ ተከታታይ የእንግሊዝ ሻምፒዮናው Man City

ያጋሩት

ትላንት በተጠናቀቀው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ዌስትሃምን 3-1 አሸንፏል። በዚህ ድል “ሲቲዜኖቹ” ባለፉት ሰባት አመታት ውስጥ ለአራተኛ ተከታታይ የእንግሊዝ ሻምፒዮና ሲሆኑ እንደ አጠቃላይ ሲታይ ደሞ ስድስተኛ ዋንጫቸውን አንስተዋል።

የጨዋታው ውጤት በመጀመሪያዎቹ 20 ደቂቃዎች ውስጥ ነበር የተወሰነ የመሰለው። የፕሪሚየር ሊጉ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠው ፊል ፎደን ሁለት ጎሎችን አስቆጠረ። ሆኖም ከእረፍት በፊት ኩዱስ ባስደናቂ ምት ያስቆጠረው ግብ የዌስትሃምም አልፎም የአርሰናልም ተስፋ በህይወት እንዲቆይ አድርጓል። ጭዋታው ማን ሲተ ሁለት ዌስትሃም አንድ በሆነ ውጤት ወደ እረፍት ገቡ።

በሁለተኛው አጋማሽ ሮድሪ ከርቀት መቶ ያስቆጠረው ጎል ሲቲ የፕሪሜርሊጉ ሻምፒዮና እንደሆነ ያረጋገጠ ነበር። ስታዲየሙ ከመጨረሻው ፊሽካ በኋላ ከቡድኑ ጋር በደስታ ፈንድቷል።

ለሲቲ ይህ የፕሪሜርሊጉ ሻምፒዮናነት ማዕረግ ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ አራተኛውን ተከታታይ ባጠቃላይ ስድስተኛውን ሆኖለቷል። ከዚህ ቀደም የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን በተከታታይ ለአራት ጊዜ ማሸነፍ የቻለ ቡድን አልነበረም።

ከ2016 ጀምሮ በሲቲ መሪነት የቆየው ጋርዲዮላ ለስድስተኛው ጊዜ ነው ዋንጫውን እያነሳ ያለው። በፕሪሜርሊጉ ታሪክ ስድስት ጊዜ ዋንጫውን ካሸነፉ አሰልጣኞች አራተኛው አሰልጣኝ ያደርገዋል። ከዚህ በፊት አሌክስ ፈርጉሰን (13)፣ ጆርጅ ራምሴ (6) እና ቦብ ፓይስሊ (6) ጊዜ የሊጎን ዋንጫ አንስተውቷል።

በተጨማሪም በግንቦት 25 2024 የጋርዲዮላ ቡድን በኤፍኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድን ይገጥማል።

Manchester City — West Ham — 3:1
Goals: Foden 2, 18, Rodri 59 — Kudus 42.


ያጋሩት