ባርሴሎና የማንቸስተር ሲቲውን አጥቂ ኤርሊንግ ሃላንድን እየተመለከተ ነው እና ይሄንን ዝውውር እውን ለማድረግ ሶስት ወዳኝ ተጫዋቾችን መሸጥ ሊያስፈልገው ይችላል። በ2022 ሀላንድ ከማንቸስተር ሲቲ ከቦርሺያ ዶርትሙንድ ከተዘዋወረ በኋላ ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። ከክለቡ ጋር ምንም እንኳን ከሁለት አመት በታች ቢቆይም ስለወደፊቱ ክሉቡ ውሬዎች አሉ። ሪያል ማድሪድ እንዲሁ ፍላጎት አለው፣ እና ኬሊያን ምባፔን ማስፈረም ካልቻሉ ወደ ሃላንድ ሊዞሩ ይችላሉ።
ባርሴሎና ምንም እንኳን የፋይናንስ ችግር ቢኖርም ሃላንድን ወደ ካምፕ ኑ ለማምጣት ከፍተኛ ፍላጎት አለው። ፕሬዝደንት ጆአን ላፖርታ የማንቸስተር ሲቲውን ኮከብ የማስፈረም የረዥም ጊዜ ህልም አላቸዉ እና ይህን ለማድረግም ሶስት ወሳኝ ተጫዋቾችን ለመሸጥ ተዘጋጅተዋል። በጥያቄ ውስጥ ያሉት ተጫዋቾች ራፊንሃ፣ ጁልስ ኩንዴ እና ሮበርት ሌዋንዶውስኪ ናቸው። ራፊንሃ የባርሴሎናውን አሰልጣኝ ዣቪ ትዕግስት እየፈተነ ሲሆን ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንደሚመለስም እየተነገረ ነው። ኩንዴ እንደተጠበቀው እያደረገ አይደለምግ, እና እሱን መሸጥ ለባርሴሎና ጥሩ የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ ይችላል። ስለ ሌዋንዶውስኪ ፣ አቋም ወድቋል ፣ እና ቀደም ሲል ከሳውዲ አረቢያ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ቢያደርግም ባርሴሎና የሃላንድን ፊርማ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ያንን አማራጭ ከግምት ማስገናት ሊኖርበት ይችላል።